• የጥቅምት 28 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Nov 7 2024
    ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የወረዳ ባለሥልጣናትን ጨምሮ 48 ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ አስታወቀ። የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በእገታና በዘረፋ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ክ129 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጠ። የጀርመን የፋይናንስ ሚኒስትር ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ጥምር መንግሥት ቀውስ ውስጥ ገብቷል። ተቃዋሚዎች አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ግፊት እያደረጉ ነው። ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር የጥምር መንግሥቱ ለገባበት ቀውስ መፍትሄ ለማምጣት ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድ እንዲኖር ፖለቲከኞቹን አሳስበዋል።
    Show More Show Less
    10 mins
  • የረቡዕ፤ ጥቅምት 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    10 mins
  • የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    Nov 5 2024
    DW Amharic አርስተ ዜና በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት አሜሪካ አስታወቀች። በኢትዮጵያ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው፤ የሚል አቋም እንዳላትም ገልፃለች።--አሜሪካ 47 ኛዉን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን እያካሄደች ነዉ። ሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች በየፊናቸዉ እንደሚያሸንፉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአሜሪካ የደኅንነት ባለስልጣናት «የውጭ ኃይሎች» ያሏቸዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እምነት እንዲያጣ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲሉ እየከሰሱ ነዉ።--የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ 11,000 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩስያ ድንበር ኩርስክ ግዛት መግባታቸዉን በስጋት ገለፁ።
    Show More Show Less
    11 mins
  • የጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Nov 4 2024
    በሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሹ ላይ አሸባብ ባደረሰው ጥቃት የተመድ ሠራተኞችን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸው ተነገረ። ጥቃቱ የደረሰው ከመቃዲሹ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት ስፍራ ነው። ስፔን ውስጥ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ዛሬም የጎርፍ ሰለባዎችን መፈለግ ቀጥለዋል። ቫለንሲያ ግዛት በጎርፍ ከደረሰባት አደጋ ጋር እየታገለች ዛሬ ኃይለኛ ዝናብ የወረደባት ባርሴሎና ከተማ በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች። የሱዳን ጦር አዛዥ አብደልፈታህ አል ቡርሀን የባለሥልጣናት ሹም ሽር አደረጉ። አራት አዳዲስ ሚኒስትሮችንም ሰየሙ። የእስራኤል ጦር ሰሜን ጋዛ ውስጥ የሚገኘው የክትባት ማዕከል ላይ ጥቃት አላዳረስኩም አለ።
    Show More Show Less
    9 mins
  • የጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    11 mins
  • የጥቅምት 23 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    Nov 2 2024
    የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች 120 የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ አለ። ህወሓት በፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት የገባቸውን ግዴታዎች እየፈጸመ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሰሰ። አሜሪካ “ታሪካዊ“ ያለችው “የርስ በርስ ጦርነት ያቆመ ሥምምነት“ የተፈረመበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዋንኛ የሕብረተሰብ ጤና ተግዳሮት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ከታኅሳስ 22 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ብቻ 7.3 ሚሊዮን የወባ ሕሙማን መመዝገባቸውን፤ 1157 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።
    Show More Show Less
    12 mins
  • የጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Nov 1 2024
    *በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት ቢያንስ የ40 ንጹሃን ሰዎች ህይወት አለፈ። *በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዛሬ ጠዋት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ ፡፡ *ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች በልዩነታቸው ላይ ለመነጋገር እንደተስማሙ ተነገረ። *የጀርመን ፌደራል መንግስት በሀገሩ የሚገኙ የኢራን ቆንስላዎች በሙሉ እንዲዘጉ ወሰነ። * እስራኤል ሊባቦስ እና ጋዛ ውስጥ ጥቃት ሰነዘረች
    Show More Show Less
    10 mins
  • የሐሙስ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    Oct 31 2024
    DW Amharic -በአማራ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የሰላም ጥረት አለመሳካቱን ጠቅላይ ሚንስትሩ መግለፃቸው-ከአየር ንብረት እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ጋር ተዳምሮ የግጭት መስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ችግር ዳርጓል መባሉ-ሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ የሽግግር ተልዕኮ ለማቋቋም መወሰኑን ማወደሷ-እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ በፈፀመችው የአየር ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ መባሉ-ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ የባሊስቲክ ሚሳኤል መተኮሷን መግለጿ በዛሬው የዓለም ዜና የተካተቱ ርዕሶች ናቸው።
    Show More Show Less
    11 mins